ማቴዎስ 23:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ የአባቶቻችሁን ጅምር ተግባር ከፍጻሜ አድርሱ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ፈጽሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲያውስ አባቶቻችሁ የጀመሩትን እናንተም ፈጽሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ። |
ታላቅና ኀያል አምላክ ሆይ! ለብዙ ሺህ ምሕረትን ታደርጋለህ፤ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ።
ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ አባቶቻቸውም ከአደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።
እነሆም፥ የእግዚአብሔርን መዓት በእስራኤል ላይ አብዝታችሁ ትጨምሩ ዘንድ እናንተ በኀጢአተኞች ሰዎች በደል በአባቶቻችሁ ፋንታ ተነሥታችኋል።