ማቴዎስ 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀሩትም ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው፤ ገደሉአቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀሩትም ባሮቹን በመያዝ አጕላልተው ገደሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀሩትም ባርያዎቹን ይዘው ሰደቡአቸው፤ ገደሉአቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀሩትም ደግሞ አገልጋዮቹን ይዘው በማዋረድ ደበደቡና ገደሉአቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀሩትም ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው ገደሉአቸውም። |
በዚያ ወራትም በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ከሐዋርያትም በቀር ሁሉም በይሁዳና በሰማርያ ባሉ አውራጃዎች ሁሉ ተበተኑ።
ከእነርሱ ጋር አብራችኋቸው እንደ ታሰራችሁ ሆናችሁ እስረኞችን ዐስቡ፤ መከራ የጸናባቸውንም በሥጋችሁ ከእነሱ ጋር እንዳላችሁ ሆናችሁ ዐስቡ።