ማቴዎስ 20:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጀመሪያ የተቀጠሩት ሲቀርቡ ብልጫ ያለው ክፍያ የሚያገኙ መስሏቸው ነበር፤ ነገር ግን እነርሱም አንዳንድ ዲናር ተከፈላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጀመሪያ የመጡትም በቀረቡ ጊዜ የበለጠ የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፊት የተቀጠሩት በቀረቡ ጊዜ ይበልጥ የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ ነገር ግን እነርሱም እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። |
ተቀብለውም ‘እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፤ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው፤’ ብለው በባለቤቱ ላይ አንጕኦራጕኦሩ።