ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና “እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።
ይህን ሲሰሙ፣ ደቀ መዛሙርቱ እጅግ በመገረም፣ “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” ሲሉ ጠየቁ።
ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።
ደቀ መዛሙርቱ ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ተገረሙና “ታዲያ፥ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።
ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና፦ እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል? አሉ።
ዳግመኛም እላችኋለሁ፤ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል፤” አለ።
ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል፤” አላቸው።
እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።
ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ።
“የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”