ማቴዎስ 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ኢየሱስ “ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና” አለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “ሕፃናት ወደ እኔ እንዲመጡ ፍቀዱላቸው፤ አትከልክሏቸውም፤ መንግሥተ ሰማይ እንደ እነዚህ ላሉት ናትና” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ኢየሱስ እንዲህ አለ “ሕፃናቱን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም እንዲመጡ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም፦ “መንግሥተ ሰማይ እንደነዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሉአቸው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ኢየሱስ፦ ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ፤ |
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ በአእምሮ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃናት ሁኑ፤ በዕውቀትም ፍጹማን ሁኑ።
እርሱም፦ እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ እንግዲህ የወይን ጠጅንና የሚያሰክር መጠጥን አትጠጪ፥ ርኩስ ነገርንም አትብዪ፤ ልጁ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አለኝ” ብላ ተናገረች።
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።
ሐና ግን ከእርሱ ጋር አልወጣችም። ለባልዋም፥ “ሕፃኑን ጡት እስከ አስጥለው፥ ከእኔም ጋር እስኪወጣና በእግዚአብሔር ፊት እስኪታይ ድረስ አልወጣም፤ በዚያም ለዘለዓለም ይኖራል” ብላዋለችና።
እርስዋም ከእርሱ ጋር አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ እንጀራ፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴሎም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት ገባች። ልጃቸውም ከእነርሱ ጋር ነበረ።