ማቴዎስ 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን “ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ከተሰጣቸው በቀር ይህን ትምህርት ማንም ሊቀበል አይችልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን እንዲህ አላቸው “ይህ ንግግር የተሰጠው ካልሆነ በስተቀር ሁሉም አይቀበለውም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ልዩ ችሎታ ለተሰጣቸው ነው እንጂ ይህ ነገር ለሁሉም አይሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን፦ ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤ |
በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፤ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፤ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው።”
ነገር ግን ሁሉ እግዚአብሔር እንደ አደለው፥ ሁሉም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ እንዲህ ሥርዐት እንሠራለን።
ይህንም የምላችሁ እንዲጠቅማችሁ ነው፤ ላጠምዳችሁ ግን አይደለም፤ ኑሮአችሁ አንድ ወገን እንዲሆንና እግዚአብሔርን ያለመጠራጠር እንድታገለግሉት ነው እንጂ።