ማቴዎስ 16:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም “እንጀራ ባንይዝ ነው፤” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እርስ በርሳቸው፣ “እንጀራ ስላልያዝን ነው” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እርስ በርሳቸው “እንጀራ ስላልያዝን ነው” ብለው አሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “ይህን ማለቱ ምናልባት እንጀራ ስላልያዝን ይሆናል” በማለት እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ እንጀራ ባንይዝ ነው ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ። |
ኢየሱስም አውቆ እንዲህ አላቸው “እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እንጀራ ስለ ሌላችሁ ስለ ምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ? ገና አታስተውሉምን?
የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው?” አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ “ ‘ከሰማይ’ ብንል ‘እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤