La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 15:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆም ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል፤” ብላ ጮኸች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንዲት ከነዓናዊት ሴት ከዚያ አካባቢ ወጥታ፣ “ጌታ ሆይ፤ የዳዊት ልጅ፤ ራራልኝ፤ ልጄ በጋኔን ክፉኛ ተይዛለች” ብላ ጮኸች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ አንዲት ከነዓናዊት ሴት ከዚያ አገር መጥታ “የዳዊት ልጅ ጌታ ሆይ ማረኝ፤ ሴት ልጄ በጋኔን ክፉኛ ተይዛለች” እያለች ጮኸች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም አንዲት ከነዓናዊት ሴት ወደ ኢየሱስ መጥታ፥ “የዳዊት ልጅ ጌታ ሆይ! ልጄ በርኩስ መንፈስ ተይዛ ትሠቃያለችና እባክህ ራራልኝ!” እያለች ጮኸች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆም፥ ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 15:22
19 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጠ​ራ​ሁት ጊዜ ጽድ​ቄን ሰማኝ፥ ከጭ​ን​ቀ​ቴም አሰ​ፋ​ልኝ፤ ይቅር አለኝ፥ ጸሎ​ቴ​ንም ሰማኝ።


ድውይ ነኝና አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ አጥ​ን​ቶቼ ታው​ከ​ዋ​ልና ፈው​ሰኝ።


ንግ​ግ​ራ​ቸው ልዩ ወደ ሆነ፥ ቋን​ቋ​ቸ​ውም ሌላ ወደ ሆነ፥ ቃላ​ቸ​ው​ንም ታውቅ ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ቻ​ልህ ሕዝብ አል​ላ​ክ​ሁ​ህም። ወደ እነ​ዚ​ያስ ልኬህ ቢሆን ኖሮ በሰ​ሙህ ነበር።


የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።


እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት፤” እያሉ ለመኑት።


“ጌታ ሆይ! ልጄን ማርልኝ፥ በጨረቃ እየተነሣበትክፉኛ ይሣቀያልና፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ብዙ ጊዜም በውሃ ይወድቃልና።


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረን፤” ብለው እየጮሁ ተከተሉት።


ድም​ጻ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው፥ “ጌታ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ እዘ​ን​ልን” አሉ።


ቀራጩ ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ሊያ​ነሣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ደረ​ቱ​ንም እየ​መታ፦ ‘አቤቱ፥ እኔን ኀጢ​ኣ​ተ​ኛ​ውን ይቅር በለኝ’ አለ።


ክፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ያደ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ይፈ​ወሱ ነበር።