ማቴዎስ 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይመነጫል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአፍ የሚወጣው ግን ከልብ ይወጣል፤ እነዚህ ሰውን ያረክሱታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአፍ የሚወጣው ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውን የሚያረክሰውም እርሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው። |
የጻድቃን ልብ ታማኝነትን ይማራል፤ የኃአጥኣን አፍ ግን ክፋትን ይመልሳል። የደጋግ ሰዎች መንገዶች በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደዱ ናቸው፥ ስለ እነርሱም ጠላቶች ወዳጆችን ይሆናሉ።
ጌታውም እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፥ ያልዘራሁትን የማጭድ፥ ያልበተንሁትንም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? እንደ ቃልህ እፈርድብሃለሁ።
እግዚእብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፤ እግዚአብሔርም አንተን ይበቀልልኝ፤ እጄ ግን በአንተ ላይ አትሆንም።