ማቴዎስ 14:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልብሱንም ጫፍ ብቻ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሽተኞቹ የልብሱን ጫፍ ብቻ ይነኩ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልብሱን ጫፍ ብቻ ለመንካት ለመኑት፤ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሽተኞቹም የልብሱን ጫፍ ብቻ እንዲነኩ ለመኑት። የነኩትም ሁሉ ከበሽታቸው ተፈወሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የልብሱንም ጫፍ ብቻ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ። |
በገባበትም ስፍራ ሁሉ፥ መንደርም ከተማም ገጠርም ቢሆን፥ በገበያ ድውዮችን ያኖሩ ነበር፤ የልብሱንም ጫፍ እንኳ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ።
የሙሴ ሕግ እንዳይሻር ሰው በሰንበት የሚገዘር ከሆነ እንግዲያ ሰውን ሁለንተናውን በሰንበት ባድነው ለምን ትነቅፉኛላችሁ?
ስሙን በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፤ እርሱንም በማመን በፊታችሁ ይህን ሕይወት ሰጠው።