ማቴዎስ 12:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይከራከርም፤ አይጮህምም፤ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይጨቃጨቅም ወይም አይጮኽም፤ ድምፁም በአደባባይ አይሰማም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይከራከርም አይጮህምም፤ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ አይከራከርም ወይም አይጮኽም፤ በመንገዶችም ላይ ድምፁን የሚሰማ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። |
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
ፈሪሳውያንም “የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?” ብለው ጠየቁት፤ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔ ጳውሎስ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ብርቅ ግን የምደፍራችሁ በክርስቶስ የዋህነትና ቸርነት እማልዳችኋለሁ፥ በፍቅራችሁ እታመናለሁና።