La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 10:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደቀ መዝሙር መምህሩን፣ ባሪያም ጌታውን ከመሰለ ይበቃዋል። ባለቤቱን ‘ብዔልዜቡል’ ካሉት፣ ቤተ ሰዎቹንማ እንዴት አብልጠው አይሏቸውም!

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ደቀመዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባርያም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔልዜቡል ካሉት፥ ቤተሰቦቹንማ እንዴት ከዚህ የበለጠ አይሉአቸው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ተማሪ እንደአስተማሪው፥ አገልጋይም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። የቤቱን ጌታ ‘ብዔልዜቡል’ ብለው ከጠሩት ቤተሰቦቹንማ ከዚህ በከፋ ስም እንዴት አይጠሩአቸውም!

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!

Ver Capítulo



ማቴዎስ 10:25
13 Referencias Cruzadas  

አካ​ዝ​ያ​ስም በሰ​ማ​ርያ በሰ​ገ​ነቱ ላይ ሳለ በዐ​ይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እር​ሱም፥ “ሂዱ፥ ከዚህ ደዌ እድን እንደ ሆነ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ጠይቁ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊጠ​ይ​ቁ​ለት ሄዱ።


ፈሪሳውያን ግን ሰምተው “ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም፤” አሉ።


እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።


ፈሪሳውያን ግን “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” አሉ።


እነርሱም “እንችላለን፤” አሉት። ኢየሱስም “እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤


ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም “ብዔል ዜቡል አለበት፤” ደግሞ “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” ብለው ተናገሩ።


ነገር ግን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው፥ “በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣ​ቸ​ዋል” ያሉ ነበሩ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ሰይ​ጣን ሰይ​ጣ​ንን ማው​ጣት እን​ደ​ምን ይቻ​ለ​ዋል?” አላ​ቸው።


ሰይ​ጣ​ንስ እርስ በርሱ ከተ​ለ​ያየ መን​ግ​ሥቱ እን​ዴት ይጸ​ናል? በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣል ትላ​ላ​ች​ሁና።


እኔ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን የማ​ወጣ ከሆነ፥ ልጆ​ቻ​ችሁ በምን ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል? ስለ​ዚህ እነ​ርሱ ይፋ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል።


ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ​ዎች፥ “ጋኔን ይዞት ያብ​ዳል፤ ለም​ንስ ታዳ​ም​ጡ​ታ​ላ​ችሁ?” አሉ።


ሕዝ​ቡም፥ “ጋኔን አለ​ብ​ህን? ማን ሊገ​ድ​ልህ ይሻል?” ብለው መለ​ሱ​ለት።


አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ ሳም​ራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔ​ንም እንደ አለ​ብህ መና​ገ​ራ​ችን በሚ​ገባ አይ​ደ​ለ​ምን?” ብለው ጠየ​ቁት።


አይ​ሁ​ድም እን​ዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እን​ዳ​ለ​ብህ ዐወ​ቅን፤ አብ​ር​ሃም ስንኳ ሞቶ​አል፤ ነቢ​ያ​ትም ሞተ​ዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚ​ጠ​ብቅ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሞትን አይ​ቀ​ም​ስም ትላ​ለህ።