ማርቆስ 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕዝቡ አንዱ መልሶ “መምህር ሆይ! ድዳ መንፈስ ያደረበትን ልጄን ወደ አንተ አምጥቼአለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው እንዲህ አለው፤ “መምህር ሆይ፤ ርኩስ መንፈስ ዐድሮበት ድዳ የሆነውን ልጄን ወደ አንተ አምጥቼዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው እንዲህ አለው፤ “መምህር ሆይ፤ ርኩስ መንፈስ አድሮበት ዲዳ የሆነውን ልጄን ወደ አንተ አምጥቼዋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕዝቡም መካከል አንዱ፥ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “መምህር ሆይ፥ ድዳ በሚያደርግ መንፈስ የተያዘውን ልጄን ወደ አንተ አምጥቼዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሕዝቡ አንዱ መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ ዲዳ መንፈስ ያደረበትን ልጄን ወደ አንተ አምጥቼአለሁ፤ |
በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፋጫል፤ ይደርቃልም፤ እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፤ አልቻሉምም” አለው።
ኢየሱስም ሕዝቡ እንደ ገና ሲራወጥ አይቶ ርኵሱን መንፈስ ገሠጸና “አንተ ድዳ ደንቆሮም መንፈስ፥ እኔ አዝሃለሁ፤ ከእርሱ ውጣ! ከእንግዲህም አትግባበት፤” አለው።
አንድ ሰውም በሕዝቡ መካከል ጮኾ እንዲህ አለው፥ “መምህር ሆይ፥ እርሱ ለእኔ አንድ ነውና ልጄን ታይልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።
እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ ሄደ፤ ሊሞት ቀርቦ ነበርና ወርዶ ልጁን ያድንለት ዘንድ ለመነው፤