ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ የዋሁና ወደ ጸጥተኛው፥ ከቃሌም የተነሣ ወደሚንቀጠቀጥ ሰው ከአልሆነ በቀር ወደ ማን እመለከታለሁ?
ማርቆስ 7:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም “ስለዚህ ቃልሽ ሂጂ፤ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቶአል፤” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ስለዚህ ይህን ስላልሽ ሂጂ፤ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቷል” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “ስለዚህ ይህን ስላልሽ ሂጂ፤ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቷአል” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኢየሱስ፥ “በዚህ አነጋገርሽ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቶአል፤ እንግዲህ ወደ ቤትሽ ሂጂ!” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ስለዚህ ቃልሽ ሂጂ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቶአል አላት። |
ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ የዋሁና ወደ ጸጥተኛው፥ ከቃሌም የተነሣ ወደሚንቀጠቀጥ ሰው ከአልሆነ በቀር ወደ ማን እመለከታለሁ?