ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው መጡ፤ በድኑንም ወስደው ቀበሩት።
የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትም ይህን እንደ ሰሙ መጡ፤ ሬሳውንም ወስደው ቀበሩት።
የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ይህን በሰሙ ጊዜ መጡና በድኑን ወስደው ቀበሩት።
ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው መጡ በድኑንም ወስደው ቀበሩት።
ከእስራኤልም ጋር፥ ከእግዚአብሔርና ከቤቱም ጋር መልካም ሠርቶአልና በዳዊት ከተማ ከነገሥታቱ ጋር ቀበሩት።
ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው በድኑን ወሰዱና ቀበሩት፤ መጥተውም ለኢየሱስ አወሩለት።
ራሱንም በወጭት አምጥቶ ለብላቴናይቱ ሰጣት፤ ብላቴናይቱም ለእናትዋ ሰጠች።
ሐዋርያትም ወደ ኢየሱስ ተሰብስበው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት።
እስጢፋኖስንም ደጋግ ሰዎች አንሥተው ቀበሩት፤ ታላቅ ልቅሶም አለቀሱለት።