በመቃብርም መካከል የሚተኙ፥ በዋሻ ውስጥ የሚያልሙ፥ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። የመሥዋዕታቸውን ደምና ዕቃቸውንም ሁሉ ያረክሳሉ።
ማርቆስ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከታንኳይቱም በወጣ ጊዜ፥ ርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ወዲያው ተገናኘው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ከጀልባ እንደ ወረደ፣ ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው ከመቃብር ቦታ ወጥቶ ሊገናኘው ወደ እርሱ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ከጀልባ እንደ ወረደ፥ ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው ከመቃብር ቦታ ወጣና ወደ እርሱ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ከጀልባው እንደ ወረደ አንድ በርኩስ መንፈስ የተያዘ ሰው ወዲያውኑ ከመቃብር ቦታ ወጥቶ ተገናኘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከታንኳይቱም በወጣ ጊዜ፥ ርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ወዲያው ተገናኘው፤ |
በመቃብርም መካከል የሚተኙ፥ በዋሻ ውስጥ የሚያልሙ፥ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። የመሥዋዕታቸውን ደምና ዕቃቸውንም ሁሉ ያረክሳሉ።
ደግሞም በባሕር ዳር ሊያስተምር ጀመረ። እጅግ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ ስለ ተሰበሰቡ እርሱ በታንኳ ገብቶ በባሕር ላይ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕር ዳር በምድር ላይ ነበሩ።
ወደ ምድርም በወረዱ ጊዜ ጋኔን ያደረበት ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ልብሱንም ከጣለ ብዙ ዘመን ሆኖት ነበር፤ በመቃብር ብቻ ይኖር ነበር እንጂ ወደ ቤት አይገባም ነበር፤
ሲያመጣውም ጋኔኑ ጣለውና አፈራገጠው፤ ጌታችን ኢየሱስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠጸው፤ ልጁንም አዳነው፤ ለአባቱም ሰጠው። ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ አደነቁ።