ማርቆስ 11:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ “‘ከሰማይ ነው፤’ ብንል ‘እንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “ ‘ከሰማይ ነው’ ብንል፣ ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “ከሰማይ ነው” ብንል፥ “ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?” ይለናል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “እንግዲህ ምን እንበል?” በማለት እርስ በርሳቸው ተመካከሩ፤ “ ‘ከእግዚአብሔር ነው፥’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ፦ ከሰማይ ነው ብንል፦ እንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤ |
ምስክሩ ዮሐንስ ስለ እርሱ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ፤ እንዲህም አለ፥ “እኔ ስለ እርሱ ከእኔ በፊት የነበረ ከእኔ በኋላ ይመጣል ያልኋችሁ ሰው ይህ ነው፥ እርሱ ከእኔ አስቀድሞ ነበረና።”
በማግሥቱም ዮሐንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታችን ኢየሱስን አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓለሙን ኀጢኣት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።