ማርቆስ 1:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርኵሱም መንፈስ አንፈራገጠውና በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእርሱ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርኩሱም መንፈስ ሰውየውን በኀይል ካንፈራገጠው በኋላ እየጮኸ ከርሱ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርኩሱም መንፈስ ሰውየውን በኃይል ካንፈራገጠው በኋላ እየጮኸ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርኩሱ መንፈስ ሰውየውን ጥሎ ካንፈራገጠው በኋላ በታላቅ ድምፅ እየጮኸ ከእርሱ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርኵሱም መንፈስ አንፈራገጠውና በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእርሱ ወጣ። |
ሁሉም “ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው?” ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።
ከእርሱ የሚበረታው ቢመጣና ቢያሸንፈው ግን፥ ይታመንበት የነበረውን የጦር መሣሪያውን ይገፈዋል፤ የማረከውንና የዘረፈውን ገንዘቡንም ይወስዳል።
እነሆ፥ ጋኔን ሊነጥቀኝ ነው፤ ድንገትም ያስጮኸዋል፤ ጥሎም ያፈራግጠዋል፤ አረፋም ያስደፍቀዋል፤ ቀጥቅጦ በጭንቅ ይተወዋል።
ሲያመጣውም ጋኔኑ ጣለውና አፈራገጠው፤ ጌታችን ኢየሱስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠጸው፤ ልጁንም አዳነው፤ ለአባቱም ሰጠው። ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ አደነቁ።