ዓሣ አጥማጆችም ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ በዚያ ይቆማሉ። ያም መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።
ማርቆስ 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ፤” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “ተከተሉኝ፤ ሰው አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም፥ “ተከተሉኝ፤ ሰው አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም፦ “ኑ ተከተሉኝ፤ ዓሣን እንደምታጠምዱ ሁሉ ሰዎችንም እንድትሰበስቡልኝ አደርጋችኋለሁ፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። |
ዓሣ አጥማጆችም ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ በዚያ ይቆማሉ። ያም መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።
እንዲሁም የስምዖን ባልንጀራዎች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ ተደነቁ፤ ጌታችን ኢየሱስም ስምዖንን፥ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህስ ሰውን ታጠምዳለህ” አለው።