ሉቃስ 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልያስ ተገለጠ የሚሉም ነበሩ፤ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል የሚሉም ነበሩና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎች ኤልያስ እንደ ተገለጠ፣ ሌሎች ደግሞ ከቀድሞዎቹ ነቢያት አንዱ ከሙታን እንደ ተነሣ ይናገሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎችም “ኤልያስ ተገለጠ፤” ሌሎችም “ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል፤” ይሉ ስለ ነበር ግራ ተጋባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም አንዳንዶቹ “ነቢዩ ኤልያስ ተመልሶ መጥቶአል፤” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “ከቀድሞዎቹ ነቢያት አንዱ ከሞት ተነሥቶአል፤” ይሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሐንስ ከሙታን ተነሣ፥ ሌሎችም፦ ኤልያስ ተገለጠ፥ ሌሎችም፦ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል ይሉ ስለ ነበሩ አመነታ። |
እነርሱም መልሰው፥ “መጥምቁ ዮሐንስ ነው የሚሉህ አሉ፤ ኤልያስ ነው የሚሉህም አሉ፤ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል የሚሉህም አሉ” አሉት።
“እንኪያ አንተ ማነህ? አንተ ኤልያስ ነህን?” ብለው ጠየቁት፤ “አይደለሁም” አለ፤ “እንኪያ አንተ ነቢዩ ነህን?” አሉት፤ “አይደለሁም” አለ።