ሉቃስ 9:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም፥ “አትከልክሉት፤ ባለጋራችሁ ካልሆነ ባልንጀራችሁ ነውና” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “አትከልክሉት፤ የማይቃወማችሁ ሁሉ እርሱ ከእናንተ ጋራ ነውና” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ግን፦ “የማይቃወማችሁ ከእናንተ ጋር ነውና አትከልክሉት፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “የማይቃወማችሁ ሁሉ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነ ተዉ፤ አትከልክሉት!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ ግን፦ የማይቃወማችሁ ከእናንተ ጋር ነውና አትከልክሉት አለው። |
ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚችል አገልጋይ የለም፤ ካልሆነም አንዱን ይወድዳል፤ ሁለተኛውንም ይጠላል፤ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል፤ ለሁለተኛውም እንቢ ይላል፤ እንዲሁም እናንተ ገንዘብ እየወደዳችሁ ለእግዚአብሔር መገዛት አትችሉም።”
ስለዚህም ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፥ “ኢየሱስ ውጉዝ ነው” የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው” ሊል አንድስ እንኳን እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።