ሉቃስ 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ብቻውን ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱም ከእርሱ ጋር ሳሉ፥ “ሰዎች ማን ይሉኛል?” ብሎ ጠየቃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ይጸልይ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም ከርሱ ጋራ ነበሩ፤ እርሱም፣ “ሕዝቡ እኔን ማን ነው ይሉኛል?” ብሎ ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለብቻውም ሲጸልይ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ እርሱም፦ “ሕዝቡ እኔን ማን ይሉኛል?” ብሎ ጠየቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን ኢየሱስ ብቻውን ሲጸልይ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ከእርሱ ጋር ሆኑ፤ እርሱም፦ “ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል?” ሲል ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፦ ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው። |
ከዚህም በኋላ በአንዲት ቦታ ጸለየ፤ ጸሎቱን በጨረሰ ጊዜም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ አስተማራቸው ጸሎት አስተምረን” አለው።
እነርሱም መልሰው፥ “መጥምቁ ዮሐንስ ነው የሚሉህ አሉ፤ ኤልያስ ነው የሚሉህም አሉ፤ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል የሚሉህም አሉ” አሉት።
ከዚህም ነገር በኋላ በስምንተኛው ቀን ጌታችን ኢየሱስ ጴጥሮስን፥ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞአቸው ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።