La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 8:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ክፉ​ውን ጋኔን ከዚያ ሰው ላይ እን​ዲ​ወጣ ያዝ​ዘው ነበ​ርና፤ ዘወ​ት​ርም አእ​ም​ሮ​ዉን ያሳ​ጣው ነበ​ርና፤ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በእ​ግር ብረት አስ​ረው ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ እግር ብረ​ቱ​ንም ይሰ​ብር ነበር፤ ጋኔ​ኑም በም​ድረ በዳ ያዞ​ረው ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ርኩሱ መንፈስ ይህን ያለው ከሰውየው እንዲወጣ ኢየሱስ አዝዞት ስለ ነበር ነው። ርኩሱ መንፈስ በየጊዜው ስለሚነሣበት ሰውየው በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ቢጠበቅም፣ የታሰረበትን ሰንሰለት እየበጣጠሰ ያደረበት ጋኔን ወደ በረሓ ይነዳው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም የሆነው ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ከሰውዬው እንዲወጣ አዞት ስለ ነበረ ነው። ለብዙም ጊዜ ይዞት ነበርና፤ በሰንሰለትና በእግር ብረትም ታስሮ ይጠበቅ ነበር፤ እስራቱንም ሰብሮ በጋኔኑ ወደ ምድረ በዳ ይወሰድ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህንንም ያለበት ምክንያት ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ከሰውየው እንዲወጣ አዞት ስለ ነበር ነው። ከዚህ በፊት ርኩሱ መንፈስ በሰውየው ላይ ብዙ ጊዜ ይነሣበት ነበር፤ በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ይጠበቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ ሰንሰለቱን ይበጥስ፥ እግር ብረቱንም ይሰብር ነበር። ጋኔኑም እየነዳ ወደ በረሓ ይወስደው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ርኵሱን መንፈስ ከሰውዬው እንዲወጣ ያዘው ነበርና። ብዙ ዘመንም ይዞት ነበርና፥ በሰንሰለትና በእግር ብረትም ታስሮ ይጠበቅ ነበር፤ እስራቱንም ሰብሮ በጋኔኑ ወደ ምድረ በዳ ይነዳ ነበር።

Ver Capítulo



ሉቃስ 8:29
9 Referencias Cruzadas  

“አንተ ርኵስ መንፈስ፥ ከዚህ ሰው ውጣ፤” ብሎት ነበርና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ባየው ጊዜ ጮኸ፤ ሮጦም ሰገ​ደ​ለት፤ “የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር ምን አለኝ?” እያ​ለም በታ​ላቅ ቃል ጮኸ፤ እን​ዳ​ያ​ሠ​ቃ​የ​ውም ማለ​ደው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ስምህ ማነው?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ እር​ሱም፥ “ስሜ ሌጌ​ዎን ነው” አለው፤ ብዙ አጋ​ን​ንት ይዘ​ውት ነበ​ርና።


እነሆ፥ ጋኔን ሊነ​ጥ​ቀኝ ነው፤ ድን​ገ​ትም ያስ​ጮ​ኸ​ዋል፤ ጥሎም ያፈ​ራ​ግ​ጠ​ዋል፤ አረ​ፋም ያስ​ደ​ፍ​ቀ​ዋል፤ ቀጥ​ቅጦ በጭ​ንቅ ይተ​ወ​ዋል።


ሲያ​መ​ጣ​ውም ጋኔኑ ጣለ​ውና አፈ​ራ​ገ​ጠው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠ​ጸው፤ ልጁ​ንም አዳ​ነው፤ ለአ​ባ​ቱም ሰጠው። ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅ​ነት የተ​ነሣ አደ​ነቁ።