እርሱም “እምነታችሁ ወዴት አለ?” አላቸው፤ እነርሱም ፈርተው ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም፥ “ውኃም ነፋስም የሚታዘዙለት ይህ ማነው?” አሉ።
ሉቃስ 8:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህ በኋላ በገሊላ ወደብ አቅጣጫ ወዳለችው ወደ ጌርጌሴኖን ሀገር በታንኳ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ከገሊላ ባሻገር ወዳለው ወደ ጌርጌሴኖን አገር በጀልባ ተሻገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገሊላም ማዶ ወዳለችው ወደ ጌርጌሴኖን አገር ተሻገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሕሩንም ተሻግረው በገሊላ ማዶ ወደምትገኘው ወደ ጌርጌሴኖን አገር ደረሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገሊላም አንጻር ወዳለችው ወደ ጌርጌሴኖን አገር በታንኳ ደረሱ። |
እርሱም “እምነታችሁ ወዴት አለ?” አላቸው፤ እነርሱም ፈርተው ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም፥ “ውኃም ነፋስም የሚታዘዙለት ይህ ማነው?” አሉ።
ወደ ምድርም በወረዱ ጊዜ ጋኔን ያደረበት ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ልብሱንም ከጣለ ብዙ ዘመን ሆኖት ነበር፤ በመቃብር ብቻ ይኖር ነበር እንጂ ወደ ቤት አይገባም ነበር፤