ሉቃስ 8:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀርበውም፥ “መምህር ሆይ፥ መምህር ሆይ፥ ልንጠፋ ነው” ብለው ቀሰቀሱት፤ ተነሥቶም ነፋሱንና የውኃዉን ማዕበል ገሠጻቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፣ “ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ መጥፋታችን እኮ ነው!” እያሉ ቀሰቀሱት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የውሃውን መናወጥ ገሠጸ፤ በዚህ ጊዜ ነፋሱም ነውጡም ተወ፤ ጸጥታም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀርበውም፦ “መምህር ሆይ! መምህር ሆይ! እየጠፋን ነው፤” እያሉ ቀሰቀሱት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የሚናውጠውን የውኃ ሞገድ ገሠጻቸው፤ እነርሱም አቆሙ፤ ጸጥታም ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱ “መምህር ሆይ! መምህር ሆይ! ልናልቅ ነው!” ሲሉ ኢየሱስን ቀሰቀሱት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የሚያናውጠውን ማዕበል ገሠጻቸው፤ ነፋሱና የሚያናውጠው ማዕበል ወዲያውኑ ቆሙ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀርበውም፦ አቤቱ፥ አቤቱ ጠፋን እያሉ አስነሡት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የውኃውን ማዕበል ገሠጻቸው፤ ተዉም፥ ጽጥታም ሆነ። |
እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አልነበረም፤ ተጣራሁ፤ የሚመልስም አልነበረም፤ እጄ ለማዳን ጠንካራ አይደለምን? ወይስ ለማዳን አልችልምን? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዐሣዎቻቸው ይሞታሉ፤ በጥማትም ያልቃሉ።
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢትረፈረፍና ቢጮኽ ከእርሱ አያልፍም።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ዝም በልና ከእርሱ ውጣ” ብሎ ገሠጸው፤ ጋኔኑም በምኵራቡ መካከል ጣለውና ከእርሱ ወጣ፤ ነገር ግን ምንም አልጐዳውም።
ስምዖንም መልሶ፥ “መምህር፥ ሌሊቱን ሁሉ ደክመናል፤ የያዝነውም የለም፤ ነገር ግን ስለ አዘዝኸን መረቦቻችንን እንጥላለን” አለው።
እርሱም “እምነታችሁ ወዴት አለ?” አላቸው፤ እነርሱም ፈርተው ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም፥ “ውኃም ነፋስም የሚታዘዙለት ይህ ማነው?” አሉ።