እናቱና ወንድሞቹም ወደ እርሱ መጡ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ብዙ ነበርና ሊያገኙት አልቻሉም።
ከዚህ በኋላ የኢየሱስ እናትና ወንድሞቹ እርሱ ወዳለበት መጡ፤ እነርሱም ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ወደ እርሱ ሊቀርቡ አልቻሉም።
እናቱና ወንድሞቹም ወደ እርሱ መጡ፤ ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ከእርሱ ጋር ለመገናኘት አልቻሉም።
የኢየሱስ እናትና ወንድሞቹ ወደ እርሱ መጡ፤ ነገር ግን ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሊያገኙት አልቻሉም።
እናቱና ወንድሞቹም ወደ እርሱ መጡ፥ ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሊያገኙት አልተቻላቸውም።
ዘመዶቹም ሰምተው “አበደ” ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።
“እናትህና ወንድሞችህ ከውጭ ቆመዋል፤ ሊያዩህም ይሻሉ” አሉት።