ሉቃስ 6:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎ ለሚያደርጉላችሁ በጎ ብታደርጉ እንግዲህ ዋጋችሁ ምንድን ነው? እንዲህስ ኃጥኣንም ያደርጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ላደረጉላችሁ መልካም ብታደርጉ ምን የተለየ ዋጋ ታገኛላችሁ? ኀጢአተኞችም እንኳ እንደዚያ ያደርጋሉና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካምም ለሚያደርጉላችሁ መልካም ብታደርጉ ምስጋናችሁ ምንድነው? ኀጢአተኞች እንኳ ያን ያደርጋሉና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልካም ነገር ለሚያደርጉላችሁ እናንተም መልካም ነገር ብታደርጉላቸው ምን ብልጫ ታገኛላችሁ! ኃጢአተኞችም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልካምም ለሚያደርጉላችሁ መልካም ብታደርጉ፥ ምን ምስጋና አላችሁ? ኃጢአተኞች ደግሞ ያን ያደርጋሉና። |
የሚወድዱአችሁን ብቻ ብትወዱማ እንግዲህ ዋጋችሁ ምንድን ነው? ይህንስ ኃጥኣንም ያደርጋሉ፤ የሚወድዳቸውንም ይወድዳሉ።
እንዲከፍላችሁ ተስፋ ለምታደርጉት ብታበድሩ እንግዲህ ዋጋችሁ ምንድን ነው? ኃጥኣንም በአበደሩት ልክ ይከፍሉአቸው ዘንድ ለኃጥኣን ያበድራሉና።
እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ መልካምን እንዲያደርጉ፤ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፤ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው።