La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከሁ​ለቱ ታን​ኳ​ዎች ወደ አን​ዲቱ ታንኳ ወጣ፤ ይቺ​ውም ታንኳ የስ​ም​ዖን ነበ​ረች፤ “ከም​ድር ጥቂት እልፍ አድ​ር​ጋት” አለው፤ በታ​ን​ኳ​ዪ​ቱም ውስጥ ተቀ​ምጦ ሕዝ​ቡን አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከጀልባዎቹም መካከል የስምዖን ወደ ነበረችው ገብቶ፣ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ለመነው፤ ከዚያም ጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ጀመር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከታንኳዎቹም የስምዖን ወደነበረችው ወደ አንዲቱ ገብቶ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ጠየቀው፤ በታንኳይቱም ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስ ከጀልባዎቹ ወደ አንዲቱ፥ የስምዖን ወደሆነችው ገባ። ስምዖንንም “ይህችን ጀልባ ከምድር ወደ ባሕሩ እስቲ ጥቂት ፈቀቅ አድርግልኝ” አለው። ከዚህም በኋላ በጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ጀመር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከታንኳዎቹም የስምዖን ወደ ነበረች ወደ አንዲቱ ገብቶ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ለመነው፤ በታንኳይቱም ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ነበር።

Ver Capítulo



ሉቃስ 5:3
8 Referencias Cruzadas  

በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።


ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ ስለዚህም ሥቃይ ያለባቸው ሁሉ እንዲዳስሱት ይወድቁበት ነበር።


ሰዎቹም እንዳያጋፉት ታንኳን ያቆዩለት ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፤


በባ​ሕ​ሩም ዳር ሁለት ታን​ኳ​ዎች ቁመው አየ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዓሣ አጥ​ማ​ጆች መረ​ባ​ቸ​ውን ሊያ​ጥቡ ወረዱ።


በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር።