ሉቃስ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጐድጓዳው ሁሉ ይምላ፤ ተራራውም፥ ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ሰንከልካላውም የቀና ጥርጊያ ይሁን፤ ወጣ ገባው መንገድም ይስተካከል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሸለቆው ሁሉ ይሞላል፤ ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማው መንገድ ቀና፣ ወጣ ገባውም ጐዳና ለጥ ያለ ሜዳ ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጐድጓዳው ሁሉ ይሙላ፤ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ጠማማውም መንገድ ቀና ይሁን፤ ሸካራውም መንገድ የተስተካከለ ይሁን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጐድጓዳው ቦታ ሁሉ ይደልደል! ተራራና ኰረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል! ጠማማው መንገድ ይቅና! ሻካራውም መንገድ ይስተካከል! |
ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ የማያውቋትንም ጎዳና እንዲረግጡ አደርጋቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ አልተዋቸውምም።
“በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራሮችንም ዝቅ አደርጋለሁ፤ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ፤ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤
የዱር ዛፎች ሁሉ፥ ረዥሙን ዛፍ ዝቅ ያደረግሁ፥ አጭሩንም ዛፍ ከፍ ያደረግሁ፥ የለመለመውንም ዛፍ ያደረቅሁ፥ የደረቀውንም ዛፍ ያለመለምሁ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናገርሁ፤ እኔም አደረግሁ።”