ከመቃብርም ተመልሰው ለዐሥራ አንዱና ለቀሩት ባልንጀሮቻቸው ሁሉ ይህን ነገር ነገሩአቸው።
ሴቶቹ ከመቃብሩ ስፍራ ተመልሰው ይህን ሁሉ ነገር ለዐሥራ አንዱና ለተቀሩት ሁሉ ነገሯቸው።
ከመቃብሩም ተመልሰው ይህን ሁሉ ለዐሥራ አንዱና ለሌሎች ሁሉ ነገሩአቸው።
ከመቃብርም ተመልሰው ይህን ሁሉ ለዐሥራ አንዱና ለቀሩትም ነገሩአቸው።
እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤
እነዚያም መግደላዊት ማርያም፥ ዮሐና፥ የያዕቆብ እናት ማርያም፥ አብረዋቸው የነበሩት ባልንጀሮቻቸውም ይህን ለሐዋርያት ነገሩአቸው።
ቃሉንም ዐሰቡ።