እንዳያውቁትም ዐይናቸው ተይዞ ነበር።
ነገር ግን እንዳያውቁት ዐይናቸው ተይዞ ነበር።
ነገር ግን በዐይናቸው እያዩት ማን እንደ ሆነ ማወቅ አልቻሉም።
ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።
ዮሴፍም ወንድሞቹን ዐወቃቸው፤ እነርሱ ግን አላወቁትም፤ ዮሴፍም አይቶት የነበረውን ሕልም ዐሰበ።
ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤
እነርሱም ይህን ሲነጋገሩና ሲመራመሩ ጌታችን ኢየሱስ ወደ እነርሱ ቀረበ፤ አብሮአቸውም ሄደ።
ጌታችንም፥ “በትካዜ እየሄዳችሁ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩት ይህ ነገር ምንድን ነው?” አላቸው።
ዐይናቸውም ተገለጠና ዐወቁት፤ ወዲያውኑም ከእነርሱ ተሰወረ።
ይህንም ተናግራ ወደ ኋላዋ መለስ ስትል ጌታችን ኢየሱስን ቆሞ አየችው፤ ጌታችን ኢየሱስም እንደ ሆነ አላወቀችም።
በነጋ ጊዜም ጌታችን ኢየሱስ በባሕሩ ዳር ቆሞ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም አዩት፤ ግን ጌታችን ኢየሱስ እንደ ሆነ አላወቁም።