እነርሱም ይህን ሲነጋገሩና ሲመራመሩ ጌታችን ኢየሱስ ወደ እነርሱ ቀረበ፤ አብሮአቸውም ሄደ።
እየተነጋገሩና እየተወያዩ ሳሉም ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋራ ይሄድ ጀመር፤
ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤
ይህንንም በሚያወሩበትና በሚወያዩበት ጊዜ ኢየሱስ ራሱ ወደ እነርሱ ቀርቦ አብሮአቸው ይጓዝ ጀመር።
እነርሱም “እንጀራ ባንይዝ ነው፤” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።
ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።”
እርስ በርሳቸውም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ ይነጋገሩ ነበር።
እንዳያውቁትም ዐይናቸው ተይዞ ነበር።
ይህንም ሲነጋገሩ ጌታችን ኢየሱስ በመካከላቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አትፍሩ፤ እኔ ነኝ” አላቸው።