ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ በማዕድ ተቀመጠ፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱም ከእርሱ ጋር ተቀመጡ።
ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ኢየሱስ ከሐዋርያቱ ጋራ በማእድ ተቀመጠ፤
ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር በማዕድ ተቀመጠ።
የእራት ሰዓት በደረሰ ጊዜ ኢየሱስ ከሐዋርያት ጋር በማእድ ተቀመጠ።
ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር በማዕድ ተቀመጠ።
በመሸም ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።
በመሸም ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር መጣ።
ሐዋርያትም ወደ ኢየሱስ ተሰብስበው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት።
በሄዱም ጊዜ እንዳላቸው አገኙ፤ የፋሲካውንም በግ አዘጋጁ።
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “ከመከራዬ አስቀድሞ ይህን ፋሲካ ከእናንተ ጋር ልበላ እጅግ ወደድሁ።