La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚያ ሀገር እረ​ኞች ነበሩ፤ ሌሊ​ቱ​ንም ተግ​ተው መን​ጋ​ቸ​ውን ይጠ​ብቁ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያው አገር በሌሊት መንጋቸውን ሲጠብቁ በሜዳ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያም አካባቢ መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያም አካባቢ፥ በሜዳ ላይ ሌሊት መንጋቸውን እየጠበቁ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 2:8
8 Referencias Cruzadas  

ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረ​ኞች ስለ​ሌሉ፥ እረ​ኞ​ችም በጎ​ችን ስላ​ል​ፈ​ለጉ፥ እረ​ኞ​ችም ራሳ​ቸ​ውን እንጂ በጎ​ችን ስላ​ላ​ሰ​ማሩ፥ በጎች ንጥ​ቂያ ሆነ​ዋ​ልና፥ በጎ​ችም ለዱር አራ​ዊት ሁሉ መብል ሆነ​ዋ​ልና፤


የበ​ኵር ልጅ​ዋ​ንም ወለ​ደች፤ አውራ ጣቱ​ንም አሰ​ረ​ችው፤ በጨ​ር​ቅም ጠቀ​ለ​ለ​ችው፤ በበ​ረ​ትም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ በማ​ደ​ር​ያ​ቸው ቦታ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ው​ምና።


እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ቆመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በዙ​ሪ​ያ​ቸው አበራ፤ ታላቅ ፍር​ሀ​ት​ንም ፈሩ።