የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፣ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።
ሉቃስ 2:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአዩም ጊዜ የነገሩአቸው ስለዚህ ሕፃን እንደ ሆነ ዐውቀው አወሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካዩም በኋላ፣ ስለ ሕፃኑ የተነገራቸውን ገልጠው አወሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገራቸውን ቃል ገለጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕፃኑንም ካዩ በኋላ መልአኩ ስለ እርሱ የነገራቸውን አወሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ። |
የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፣ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።
ያንጊዜም ተነሥታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፤ የኢየሩሳሌምንም ድኅነት ተስፋ ለሚያደርጉ ሁሉ ስለ እርሱ ተናገረች።
እርሱ ግን፥ “ወደ ቤትህ ተመልሰህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ታላቅ ነገር ሁሉ ተናገር” ብሎ አሰናበተው። እርሱም ሄዶ በከተማዉ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ያደረገለትን ሁሉ ተናገረ።