የሚያልፈውንም ሰው ድምፅ ሰምቶ፥ “ይህ የምሰማው ምንድን ነው?” አለ።
ዐይነ ስውሩም ሕዝቡ በዚያ ሲያልፍ ሰምቶ ስለ ሁኔታው ጠየቃቸው።
ብዙ ሰዎች ሲያልፉ ሰምቶ “ይህ ምንድነው?” ብሎ ጠየቀ።
በአጠገቡ የሚያልፉትን የብዙ ሰዎች ድምፅ በሰማ ጊዜ “ይህ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ።
ሕዝብም ሲያልፍ ሰምቶ፦ ይህ ምንድር ነው? ብሎ ጠየቀ።
ከአባቱ ብላቴኖችም አንዱን ጠርቶ፦ ‘ይህ የምሰማው ምንድን ነው?’ አለው።
ከዚህም በኋላ ኢያሪኮ በደረሱ ጊዜ አንድ ዕውር በጎዳና ተቀምጦ ይለምን ነበር።
እነርሱም፥ “የናዝሬቱ ኢየሱስ ያልፋል” ብለው ነገሩት።