ሉቃስ 18:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ኢያሪኮ በደረሱ ጊዜ አንድ ዕውር በጎዳና ተቀምጦ ይለምን ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ በቀረበ ጊዜ፣ አንድ ዐይነ ስውር መንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኢያሪኮም በቀረበ ጊዜ አንድ ዐይነ ስውር በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ በቀረበ ጊዜ አንድ ዕውር ምጽዋት እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ኢያሪኮም በቀረበ ጊዜ አንድ ዕውር እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር። |
ጎረቤቶቹና ቀድሞ የሚያውቁት፥ ሲለምንም ያዩት የነበሩት ግን፥ “ይህ በመንገድ ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለም?” አሉ።
ከእናቱ ማኅፀንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተወለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ ሁልጊዜ እየተሸከሙ መልካም በሚልዋት በመቅደስ ደጃፍ ያስቀምጡት ነበር።
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።