አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ እሰበስባለሁ፣ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይነወራሉ፣ የከተማይቱም እኵሌታ ለምርኮ ይወጣል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማ አይጠፋም።
ሉቃስ 17:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም መልሰው፥ “አቤቱ፥ ወዴት ነው?” አሉት፤ እርሱም፥ “ገደላ በአለበት አሞሮች በዚያ ይሰበሰባሉ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም መልሰው፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚወሰዱት ወዴት ነው?” አሉት። እርሱም፣ “በድን ባለበት አሞሮች ይሰበሰባሉ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲመልሱለትም “ጌታ ሆይ! ወዴት ነው?” አሉት። እርሱም “ሥጋ ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ፤” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስን፥ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ነው የሚወሰዱት” ሲሉ ጠየቁት። እርሱም “በድን ባለበት አሞራዎች ይሰበሰባሉ” ሲል መለሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልሰውም፦ ጌታ ሆይ፥ ወዴት ነው? አሉት። እርሱም፦ ሥጋ ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ አላቸው። |
አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ እሰበስባለሁ፣ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይነወራሉ፣ የከተማይቱም እኵሌታ ለምርኮ ይወጣል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማ አይጠፋም።