እንዲህም አላቸው፥ “ከመካከላችሁ ወዳጅ ያለው ሰው ቢኖር በመንፈቀ ሌሊትም ወደ እርሱ ሄዶ እንዲህ ቢለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ ሦስት እንጀራ አበድረኝ።
ሉቃስ 11:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዳጄ ከመንገድ መጥቶብኛልና የማቀርብለት የለኝም።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ባልንጀራዬ ከመንገድ መጥቶብኝ የማቀርብለት ምንም ነገር የለኝምና’ ብሎ ለመነው እንበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት ምንም የለኝምና’፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዳጄ የሆነ አንድ ሰው ከሩቅ መንገድ መጥቶብኝ የማቀርብለት ምንም ምግብ የለኝም!’ ቢለው መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት የለኝምና ይላልን? |
እንዲህም አላቸው፥ “ከመካከላችሁ ወዳጅ ያለው ሰው ቢኖር በመንፈቀ ሌሊትም ወደ እርሱ ሄዶ እንዲህ ቢለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ ሦስት እንጀራ አበድረኝ።
ያ ወዳጁም ከውስጥ ሆኖ፦ ‘አትዘብዝበኝ፤ ደጁን አጥብቀን ዘግተናል፤ ልጆችም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል፤ እሰጥህ ዘንድ መነሣት አልችልም’ ይለዋልን?