ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።
ሉቃስ 11:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! የጽድቅንና የዕውቀትን መክፈቻ ወስዳችሁ ትሰውራላችሁና፤ እናንተም አትገቡምና፤ የሚገቡትንም መግባትን ትከለክሉአቸዋላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ ሕግ ዐዋቂዎች ወዮላችሁ! የዕውቀትን መክፈቻ ነጥቃችሁ ወስዳችኋልና፤ እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁበትም፤ የሚገቡትንም ከልክላችኋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ሕግ አዋቂዎች ወዮላችሁ! የዕውቀትን መክፈቻ ወስዳችኋልና፤ ነገር ግን እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁም፤ የሚገቡትንም ከለከላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ የሕግ መምህራን ወዮላችሁ! የዕውቀት በር መክፈቻ የሆነውን የእውነት ቊልፍ ይዛችኋል፤ ነገር ግን እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ወዮላችሁ ራሳችሁ አልገባችሁም የሚገቡትንም ከለከላችሁ። |
ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
እሺም አሰኛቸው፤ ሐዋርያትንም ጠርተው ገረፉአቸው፤ እንግዲህ ወዲህም በኢየሱስ ስም እንዳያስተምሩ ገሥጸው ተዉአቸው።