ሉቃስ 11:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ብርሃንህ ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በውስጥህ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳልሆነ በልብህ አስተውል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተመልከት። |
የሰውነትህ መብራት ዐይንህ ነው፤ ዐይንህ ብሩህ ከሆነ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ነው፤ ዐይንህ ታማሚ ቢሆን ግን፤ ሰውነትህ ሁሉ ጨለማ ነው።
ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ከሆነ በአንተም ላይ ምንም ጨለማ ባይኖርብህ የመብረቅ ብርሃን እንደሚያበራልህ ሁለንተናህ ብሩህ ይሆናል።”
‘ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ፤ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም፤’ የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥