ሉቃስ 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀይለኛ ሰው በጦር መሣሪያ ቤቱን የጠበቀ እንደ ሆነ ገንዘቡ ሁሉ ደኅና ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ብርቱ ሰው በሚገባ ታጥቆ ቤቱን ከጠበቀ፣ ንብረቱ በሰላም ይቀመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማናቸውም ጊዜ ኀይለኛ ሰው በሚገባ የጦር ዕቃውን ታጥቆ የራሱን ግቢ ቢጠብቅ፥ ያለው ንብረቱ በሰላም የተጠበቀ ይሆናል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ኀይለኛ ሰው የጦር መሣሪያ ይዞ ቤቱን የሚጠብቅ ከሆነ ንብረቱ በደንብ ይጠበቅለታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃይለኛ ሰው ጋሻና ጦር ይዞ የራሱን ግቢ ቢጠብቅ፥ ያለው ገንዘቡ በሰላም ይሆናል፤ |
እኔ በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆነ እንግዲህ አሁን የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።
ከእርሱ የሚበረታው ቢመጣና ቢያሸንፈው ግን፥ ይታመንበት የነበረውን የጦር መሣሪያውን ይገፈዋል፤ የማረከውንና የዘረፈውን ገንዘቡንም ይወስዳል።