አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥ፥ አትፍራቸው፤ ቃላቸውንም አትፍራ፤ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና።
ሉቃስ 11:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይስ ዕንቍላል ቢለምነው በዕንቍላል ፋንታ ጊንጥ ይሰጠዋልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይስ ዕንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ እንቁላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይስ ዕንቊላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ እንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? |
አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥ፥ አትፍራቸው፤ ቃላቸውንም አትፍራ፤ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና።
እነሆ፥ ጊንጦችንና እባቦችን፥ የጠላትንም ኀይል ሁሉ ትረግጡ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠኋችሁ፤ የሚጐዳችሁም ነገር የለም።
ከእናንተ መካከል ልጁ ዳቦ የሚለምነው አባት ቢኖር ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ ቢለምነውስ በዓሣ ፋንታ እባብን ይሰጠዋልን?
እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠትን የምታውቁ ከሆነ፥ የሰማይ አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካሙን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንዴት አብዝቶ ይሰጣቸው ይሆን?”