ካህኑም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን በመሠዊያው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል፤ ካህኑም ያስተሰርይለታል፤ እርሱም ንጹሕ ይሆናል።
ዘሌዋውያን 14:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደኅነኛዪቱንም ዶሮ ከከተማ ወደ ሜዳ ይሰድዳታል፤ ለቤቱም ያስተሰርይለታል፤ ንጹሕም ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕይወት ያለውንም ወፍ ከከተማ ወደ ውጭ ይልቀቀው፤ በዚህ ሁኔታ ለቤቱ ያስተሰርይለታል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕይወትም ያለውን ወፍ ከከተማ ወጥቶ ወደ ተንጣለለው ሜዳ እንዲበር ይለቀዋል፤ ለቤቱም ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ንጹሕ ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ በሕይወት ያለውን ወፍ ከከተማ ውጪ ወደ ሜዳ እንዲበር ይለቀዋል፤ በዚህም ዐይነት ለቤቱ የማንጻት ሥርዓት ይፈጽማል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕያውንም ወፍ ከከተማ ወደ ሜዳ ይሰድደዋል፤ ለቤቱም ያስተሰርይለታል፥ ንጹሕም ይሆናል። |
ካህኑም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን በመሠዊያው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል፤ ካህኑም ያስተሰርይለታል፤ እርሱም ንጹሕ ይሆናል።
ቤቱንም በዶሮዪቱ ደም በምንጩም ውኃ፥ በደኅነኛዪቱም ዶሮ፥ በዝግባውም ዕንጨት፥ በሂሶጱም፥ በቀዩም ግምጃ ያነጻዋል።