በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ይዞ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያመጣል፤ ለካህኑም ይሰጠዋል።
ዘሌዋውያን 14:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስምንተኛውም ቀን ያነጹት ዘንድ ወደ ካህኑ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያመጣቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነዚህንም በስምንተኛው ቀን ስለ መንጻቱ ሥርዐት ወደ ካህኑ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስምንተኛውም ቀን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በጌታ ፊት ስለ መንጻቱ እንዲሆኑ ወደ ካህኑ ያመጣቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመንጻትን ሥርዓት በሚፈጽምበት በስምንተኛው ቀን እነዚህን ሁሉ አምጥቶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ለካህኑ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስምንተኛውም ቀን ስለ መንጻት ወደ ካህኑ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያመጣቸዋል። |
በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ይዞ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያመጣል፤ ለካህኑም ይሰጠዋል።