አቤሜሌክም አሳደደው፤ በፊቱም ሸሸ፤ እስከ ከተማው በርም አደባባይ ድረስ ብዙዎች ተጐድተው ወደቁ።
ሆኖም አቢሜሌክ አሳደደው፤ እስከ መግቢያው በር ድረስ ባለው መንገድ ሲሸሹም ብዙ ሰዎች ቈስለው ወደቁ።
ሆኖም አቤሜሌክ አሳደደው፤ እስከ መግቢያው በር ድረስ ባለው መንገድ ሲሸሹም ብዙ ሰዎች ቈስለው ወደቁ።
ጋዓል ሸሸ፤ አቤሜሌክም አሳደደው፤ በከተማይቱ ቅጽር በር ላይ ሳይቀር ብዙዎች ቈሰሉ፤
አቤሜሌክም አሳደደው፥ በፊቱም ሸሸ፥ እስከ በሩም አደባባይ ድረስ ብዙዎች ተጐድተው ወደቁ።
ገዓልም በሰቂማ ሰዎች ፊት ወጣ፤ ከአቤሜሌክም ጋር ተዋጋ።
አቤሜሌክም በአሪማ ተቀመጠ፤ ዜቡልም ገዓልንና ወንድሞቹን በሰቂማ እንዳይኖሩ ከለከላቸው።