በለሷ ግን፦ ጣፋጭነቴንና መልካሙን ፍሬዬን ትቼ በዛፎች ላይ እነግሥ ዘንድ ልሂድን? አለቻቸው።
“በለስ ግን፣ ‘ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፣ እጅግ ጣፋጭና መልካም የሆነውን ፍሬዬን መስጠት ልተውን?’ አለ።
በለስ ግን፥ “ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፥ እጅግ ጣፋጭና መልካም የሆነውን ፍሬዬን መስጠት ልተውን?” አለ።
የበለስ ዛፍ ግን ‘ጣፋጭና መልካም ፍሬዬን መስጠት ትቼ በዛፎች ላይ ለመንገሥ ልሂድን?’ አላቸው።
በለሱ ግን፦ ጣፋጭነቴንና መልካሙን ፍሬዬን ትቼ በዛፎች ላይ እንድሰፍፍ ልሂድ? አላቸው።
ዛፎችም በለሲቱን፦ መጥተሽ በላያችን ንገሺልን አሉአት።
ዛፎችም ሁሉ ወይኑን፦ መጥተህ በላያችን ንገሥ አሉት።