መሳፍንት 4:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢንንም እስኪያጠፉ ድረስ በከነዓን ንጉሥ በኢያቢን ላይ የእስራኤል ልጆች እጅ እየበረታች ሄደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከነዓናዊውን ንጉሥ ኢያቢስን እስኪደመስሱ ድረስ የእስራኤላውያን ክንድ እየበረታ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከነዓናዊውን ንጉሥ ኢያቢስን እስኪደመስሱ ድረስ የእስራኤላውያን ክንድ እየበረታ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እርሱን ፈጽመው እስከሚያጠፉ ድረስ የእስራኤል ሕዝብ በያቢን ላይ እየበረቱ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢስንም እስኪያጠፉ ድረስ በከነዓን ንጉሥ በኢያቢስ ላይ የእስራኤል ልጆች እጅ እየበረታች ሄደች። |