ናዖድም ወደ እርሱ ገባ፤ እርሱም በበጋ ቤቱ ሰገነት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ” አለው። ዔግሎምም ከዙፋኑ ተነሣ፥ ቀረበውም።
መሳፍንት 3:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናዖድም ከሄደ በኋላ አገልጋዮቹ መጡ፤ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ ባዩ ጊዜ፥ “ምናልባት በበጋ ሰገነቱ ውስጥ ወገቡን ይሞክር ይሆናል” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናዖድ ከሄደ በኋላ፣ የንጉሡ አገልጋዮች ሲመጡ፣ የዕልፍኙ በር ተቈልፎ አገኙት፤ እነርሱም፣ “በውስጠኛው ክፍል እየተጸዳዳ ይሆናል” አሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤሁድ ከሄደ በኋላ፥ የንጉሡ አገልጋዮች ሲመጡ፥ የዕልፍኙ በር ተቈልፎ አገኙት፤ እነርሱም፥ “በውስጠኛው ክፍል እየተጸዳዳ ይሆናል” አሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤሁድ ከሄደ በኋላ የንጉሡ አገልጋዮች መጥተው በሮቹ እንደ ተቈለፉ አዩ፤ ነገር ግን ንጉሡ ከውስጥ በኩል በመጸዳዳት የዘገየ መሰላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናዖድም ከሄደ በኋላ ባሪያዎቹ መጡ፥ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ ባዩ ጊዜ፦ ማናልባት በሰገነቱ ውስጥ ወገቡን ይሞክር ይሆናል አሉ። |
ናዖድም ወደ እርሱ ገባ፤ እርሱም በበጋ ቤቱ ሰገነት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ” አለው። ዔግሎምም ከዙፋኑ ተነሣ፥ ቀረበውም።
እስኪያፍሩም ድረስ ቈዩ፤ የሰገነቱንም ደጅ እንዳልከፈተ ባዩ ጊዜ መክፈቻውን ወስደው ከፈቱ፤ እነሆም፥ ጌታቸው በምድር ላይ ወድቆ ሞቶም አገኙት።
ሳኦልም ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊትንና ሰዎቹንም ለመፈለግ ዋሊያዎች ወደሚታደኑባቸው ዓለቶች ሄደ።