መሳፍንት 18:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም አምስቱ ሰዎች ወደ ወንድሞቻቸው ወደ ሶራሕና ወደ እስታሔል ተመለሱ፤ ወንድሞቻቸውንም፥ “ምን አስቀምጦአችኋል?” አሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታኦል እንደ ተመለሱ ወገኖቻቸው፣ “የሄዳችሁበት ጕዳይ እንዴት ሆነ?” በማለት ጠየቋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታኦል እንደተመለሱ ወገኖቻቸው፥ “የሄዳችሁበት ጉዳይ እንዴት ሆነ?” በማለት ጠየቋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስቱም ሰዎች ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታኦል በተመለሱ ጊዜ ወገኖቻቸው፦ “ምን ወሬ አላችሁ?” ብለው ጠየቁአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ወንድሞቻቸውም ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታኦል ተመለሱ፥ ወንድሞቻቸውም፦ ምን ወሬ ይዛችኋል? አሉአቸው። |
ወንድሞቹም፥ የአባቱ ቤተ ሰቦችም ሁሉ ወረዱ፤ ይዘውም አመጡት፤ በሶሬሕና በኢስታሔል መካከል ባለው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ቀበሩት። እርሱም እስራኤልን ሃያ ዓመት ገዛቸው።
የዳንም ልጆች ከወገናቸው አምስት ጽኑዓን ሰዎች ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲመረምሩ፥ “ሂዱ ምድሪቱንም ሰልሉ” ብለው ከሶራሕና ከኢስታሔል ላኩ። እነዚያም ወደ ተራራማዉ ወደ ኤፍሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት መጥተው በዚያ አደሩ።
አምስቱም ሰዎች ሄዱ፤ ወደ ሌሳም ደረሱ፤ በውስጡም የነበሩትን ሕዝብ ተዘልለው አዩአቸው፤ እንደ ሲዶናውያንም ልማድ ጸጥ ብለው፥ ዐርፈው፥ ተዘልለውም ተቀምጠው ነበር፤ በተመዘገበች የርስታቸው ምድርም ቃልን መናገር አልቻሉም፤ ከሲዶናውያንም ርቀው ይኖሩ ነበር። ከሶርያውያንም ጋር ግንኙነት አልነበራቸውም።
እነርሱም፥ “ምድሪቱ እጅግ መልካም እንደ ሆነች አይተናል፤ ተነሡ፤ በእነርሱ ላይ እንውጣ፤ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ትሄዱ ዘንድ፥ ምድሪቱንም ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አትበሉ።